48 Comments

  1. ንጉሳችን ጭራሽ ይገርምካል ሌላ ነገር ማሰብ እየቻልኩኝ አይደለም ሙዚቃ እራሱ ከዚ አልበም ውጪ መስማት እየፈለኩኝ አይደለም እና በዚ ሰአት አይምሮዬን ስላደስክልኝ በድንግል ስም አመሰግናለው።

  2. እንዴት ይገፋ ኢትዮያዊነት ከዚህ በላይሀዘን ከዚህ በላይ መርገም ከወዴት ይመጣል😢😢😢😢😢😢😢 ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ቴዲያችን የፎከሩብንን በአንዴ እምሺክ አደረክልን ዝም ጭጭ አስባልክልን እናመሰግንሀለን ኑርልን

  3. ከወጣ አንድ ሳምንት ቢቆጠርም እዳዲስ ብርቅ የሚሆንብኝ እኔ።ቴዲ ተባረክ የሳር እንቅፋትም አይንካህ ጠላቶችህን የምታምነው ቅዱስ ሚካኤል ይዋጋልህ።የኔ የዋህ ሀገርና ህዝቡን ወዳጅ።።

  4. እኔ ኢትዮጵያ እንደ ሀገሬ ኤርትራ የዘር የሀይማኖት የቦታ ልዩነት የሌለባት ጠንካራነቷ ተመልሶ አንድነቷ ተጠብቆ በሰላም እንድትኖርልኝ እፀልያለሁ ⛪️

  5. 🎄🎄🎄🌼🌼🌼🌹🌹🌹 የጥበብ አዉራ ከያኒ መሀኒሥ የሙዚቃ ንጉሥ በጥበቡ መድረክ ለዘላለም ንገሥ

  6. ሁሌም ቅር የሚለኝ ቴዲ 200 ዓመት አለመኖሩን ሳስብ ነው ። ቀጣዩ ትውልድ እንደሱ አይነት ሰው ያስፈልገዋል ። እኔ እድለኛ የሆንኩት ግን ቴድ ሁሉንም አልበም ሲያወጣ እየተከታተልኩ ኮምኩሚያለሁ። Thanks God❤❤❤

  7. (ዘ-ሐበሻ ዜና) በአንጋፋው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እና ወከባ ህግን በጣሰ መልኩ ይበልጥ አደገኛ እርምጃ ወዳለበት ደረጃ መሸጋገሩ ተጋለጠ። የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ፣ መሳሪያ የታጠቁ እና በፌዴራል ፖሊስ ተሽከርካሪ የመጡ ታጣቂዎች፣ ሲኤምሲ አካባቢ የሚገኘውን የቴዲ አፍሮ የግል ስቱዲዮ እና ቢሮ በኃይል ሰብረው መግባታቸውን የዓይን እማኞች እና የቅርብ ምንጮች አረጋገጡ።

    ይህ ህገ-ወጥ የኃይል እርምጃ የተፈጸመው ትናንት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ወደ ስቱዲዮው ጥሶ ለመግባት የህንጻውን ጥበቃ (ዘበኛ) በከፍተኛ ሁኔታ መደብደባቸው ተገልጿል። የህግ አስከባሪ አካላት መደበኛውን የህግ አግባብ እና የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ ወደ ጎን በመተው፣ በምሽት የዜጎችን የስራ ቦታ እና የግል ንብረት በኃይል መስበራቸው የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት እና የዜጎችን ደህንነት ክፉኛ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ድርጊት ሆኗል።

    ከዚህ የኃይል እርምጃ ባሻገር የጉዳዩን አሳሳቢነት እጅግ ከፍ የሚያደርገው የተሰበረው ቢሮ ይዘት እና የተወሰዱት ንብረቶች ጉዳይ ነው። ይህ ስቱዲዮ ቴዲ አፍሮ እንደ ዋና ቢሮ የሚጠቀምበት፣ የፈጠራ ስራዎቹን የሚያዘጋጅበት፣ ለህዝብ ጆሮ ያልደረሱ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎቹ እና ግጥሞቹ የሚገኙበት፣ እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦቹን የሚጽፍበት እጅግ ሚስጥራዊ እና ጥብቅ የጥበብ ማህደር ነው። በስፍራው በርካታ እና ውድ የሆኑ አዕምሯዊ ንብረቶች የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን በወጡ አዳዲስ መረጃዎች መሰረት ሰብረው የገቡት የፖሊስ አባላት ከስቱዲዮው ውስጥ ሁለት ላፕቶፖችን፣ ስፒከሮችን፣ የሙዚቃ ማቀናበሪያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የስቱዲዮ እቃዎችን ወስደዋል። እነዚህ የተወሰዱት ላፕቶፖች እና ማቀናበሪያ መሳሪያዎች የድምጻዊውን አዳዲስ ስራዎች እና ሚስጥራዊ የጥበብ ማህደሮች የያዙ በመሆናቸው፣ በድምጻዊው አዕምሯዊ ንብረቶች ላይ የተደቀነውን አደጋ በእጅጉ አጉልቶታል።

    የህግ እና የጥበብ ዘርፍ ተንታኞች ይህንን ክስተት ተራ የንብረት ዝርፊያ ወይም ብርበራ አድርገው አይመለከቱትም። ከሰሞኑ የቴዲ አፍሮ ምክትል ማናጀር ማህሌት ሰለሞን እና የቅርብ ጓደኛ የሆኑት አቶ የሱፍ ያሲን ያለምንም ክስ በፖሊስ መታሰራቸውን ተከትሎ፣ አሁን ደግሞ በድምጻዊው የልብ ትርታ በሆነው ስቱዲዮው ላይ የተፈጸመው ይህ ጥቃት፤ ሆን ተብሎ የጥበብ ስራዎቹን ለማሰናከል፣ ያልወጡ ስራዎቹን ለመውሰድ እና በድምጻዊው ላይ ከባድ የስነ-ልቦና ጫና ለመፍጠር የተቀነባበረ ስልታዊ ጥቃት መሆኑን አጥብቀው እየተቹ ይገኛሉ። መንግስት እና የሚመለከታቸው የፌደራል ፖሊስ ኃላፊዎች፣ የጥበብ ባለሙያው አዕምሯዊ ንብረት ላይ ስለተፈጸመው አደጋ እና በህግ ስም ስለተደረገው የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው።

  8. አሁን እኔን እያስጨነቀኝ ያለው የመጀመሪያው ኮንሰርት የት እንደሚያዘጋጅ ነው እኔ ግን ዱባይ ላይ ቢሆን ደስ ይለኛል ምክንያት ብዙ ተመልካች ያገኘው እዝያ ስለሆነ

  9. የዚህ መዚቃ ትርጉሙ ……….. ለወደፊት አገር ጥሩ ሁኔታ ላይ ስትሆን በእያንዳንዱ ይድምጽ ቅጅ ሌላ ስራ የሚሰራበት መሆኑን የሚያሳይ ይመስለኛ ::: ርዕሶቹ የማይያያዙት ለዚህ ነው ::

Leave a Reply to @YonasYo-d2v Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

© 2026 Som2ny Post - Theme by WPEnjoy